Pages

Thursday, 13 June 2013

ወይ አለማወቅ ከንቱ 
 
የኛው ጉድ የሆነው አህባሽ የተባለው 
ከትምህርቶቹ በጣም የሚገርመው 
ከጠላት አብልጦ ሙስሊም መጥላቱ ነው። 
ጎዶሎ አቂዳቸው አልቀበል ያለ
በሼሃቸው ምክር ካፍር አየተባለ
አለ በየቦታው ሙስሊም የተባለ።
ቁርአን ማስተንተን ካቃታቸው ተፍስሩ 
ለምን አልሞችን መጠየቅን ፈሩ 
ቁርአን ለመካድ አንዴትስ ደፈሩ ።
ሽርክና ቢዳአ ሞልቶ በሀገሩ 
ተውህድን ለማንገስ ወንድሞች ቢጥሩ 
ካፍር አያሉአቸው አነርሱው ከፈሩ።
ሰው አላህ ትቶ ሼህ ሲያመልክ 
እወዳለሁ ብሎ እያለፈ ልክ ።
የቱ ነው ተውሂዱ ያስተማርነው ታድያ 
ካፍር አለመሆን ምንድነው መለያ።
ወላሂ አህባሽን እናጥፋ ከሀገር 
ጊዜ አንስጣቸው እንዳያልፉ ድንበር።
ከ እስላም ጠላቶች አብረው ሊያጠፉን 
እስላምን አጥፍተው ከተውሂድ ሊገፉን ።
አልላህ ይዘንላቸው 
መንገዱን ይምራቸው 
አምቢ ካሉ ደግሞ ከራህመቱ ያርቃቸው። 
አላህ ይጠብቀን በዛት በሲፋቱ ፣
አንዲህም ይኖራል አለማወቅ ከንቱ።      


                                                      ሰኔ 8/2005 ዓል     ኢምራን የህያ  ።።
                                              

No comments:

Post a Comment