Pages

Wednesday, 17 April 2013

በጠራ ጨረቃ 
በጠራ ጨረቃ በአኩለ ሌሊት ፣
አይኖቿ አያበሩ አንዴ ከዋክብት፣
"ሳማት ሳማት" አሉት፣
"አቀፍ አቀፋት ።
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን አጇን በ'ጁ ያዘ፣
ምንም አንኩአን ጡቷ አንደሾህ ቢዋጋ ፣
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ፣
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፍፊ ሲናጋ።
ዋ! ጀማሪ መሆን  ዋ! ተማሪነት ፣
ዋ! ትዛዝ መፈፀም ዋ!ምክር መስማት፣
በተራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት ።

(መንግስቱ ለማ )

No comments:

Post a Comment