** ተወርዋሪ ኮከብ **
እንደተለመደው የከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች ያለ እረፍት የእግረኞች ና የተሽከርካሪዎች ወድያ ወዲህ መናወዝ ---እላይ ታች መኳተን ያለ መሰልቸት እያስተናገዱ ነው።እኩለ ቀን ለመባልና ላለመባል በሚያስቸግር ሰዓት ከእጁ የማትጠፋውን ማስታወሻ በግራ እጁ መዳፍ እንደያዘ ታክሲ ውስጥ ሊሰጥሙ ጉጉት ላይ ካሉት በርካቶች ጋር ቆሟል።በአንድ እጁ ፀጉሩን ማፍተልተሉን አልተወም። የተንጨባረረ ፀጉሩ ሲያዩት ብዙም ከተራ አልወጣም። ሰዉ ወደየፊናው ሊሰማራ የለገሃሬ ታክሲዎች መጥፋታቸው---። ከየት መጣ የተባለ ታክስ ፊታቸው ድቅን። ሁሉም ወደሚከፈተው የታክሲው በር በሚሻሙበት ቅፅበት የ እስክንድር ስልኩ ተንጫረረች። ፈጠን ብሎ አነሳው።
" ሀሎ----ይሀው መጣሁ ታክስ አጥቼ ነው---እንደውም ታክሲ መጣ። እዛው ጠብቂኝ---" ከማለቱ የታክሲው ረዳት -----
" ምድነው ግርግሩ---ቆይ እስቲ ---" የሰማው የለም ።
"ቀፊራ ነን --- መጋላ ---አቦ ኮኔል ያዘን። "
"እኔ አልጭንም እንዴ -----" ረዳቱ። አጉረመረሙ። ተበሳጩ። ተሳደቡ።
-------------------------- ------------------------------------- ---------------------------
ፀሐዩ እየበረታ ነው።የዓለም ፋብሪካዎች በ ድሬዳዋ ሰማይ ትይዩ የተተከሉ ይመስል የ ኦዞን ንጣፍ በመቀደዷ ፀሐይ ጨክናለች ያስብላል። አሁንም ተደወለ ።አነሳው።
" እኮ እየመጣሁ ነው---ግድ የለም አልቆይም ። እሺ---" ፊቱ አጨማተረ ።የንዴት ፍሰት ከውስጡ እንደ አዋሽ ወንዝ እየተገለባበጠ የሃይሉ ብዛት ፊቱ ላይ ይፋ ወጣ። መንገደኛው እያጉረመረመ ነው።
ሰዓቱ አልጨበጥ እንዳለ ነው። ይሄዳል ---ይነጉዳል--።ሰዓቱ ከሄደ አይቀር እንደአባይ ወንዝ ግንድ ይዞ ባይዞር እንኳን እሱን ይዞት ቢሄድ ተመኘ። ሙቀቱ አይሏል ።እስክንድር የያዛት ማስታወሻ በራስ ቅሉ ከፍ አድርጎ ፀሐይቱን ለመከላከል ሞከረ። በሰፈሩ (ለገሃሬ ) የተሽከርካሪ ጩሀት ና የ ሰው ትርምስ ጋብ ብሎ ---ሰዎች በካፍቴርያ በረንዳ ላይ ሻይ ቡና እያሉ ከሰማይ የሚወርደውን አስጠሊታ ገበን ይታዘቡታል።የቆሙ ተሳፋሪዎች ታከታቸው። ተበታተኑ።
እስክንድር በአለባበሱ ብዙም አይታማም።በፀሐይ ትኩሳት የተለበለበው ሸራ ጫማው ምን ያህል ረመጥ እንደሆነበት ያስታውቃል።በንፅህናው ይሁን በእድሜው የማያስታውቅ የነተበ ጂንስ ሱሪ አድርጓል።አንገተ ክብና ቀጭን የሆነ ሹራብ ለብሷል። ክስት ባለው ፊቱ ላይ ተቆልምሞ የሚታየው አፍንጫው ዳገት ላይ ግማሽ ፊቱ የጋረደ ጥቁር መነፅር አጥልቋል። ቀስ እያለ ወደ አንድ ፑል ማጫወቻ ቤት ተጠጋ። ገባ። ቆሞ ያያል። ደክሞታል።
------------------------------ ------------------------------------ ---------------------------
ሃና ይመጣል ብላ የምትጠብቀውን እስክንድር ቆየባት። ግራ ገባት። 'እየመጣሁ ብሎኝ? ' ትላለች ለራሷ። በድጋሚ ደውለች ----
" ምነው ቀረህ --እየጠበቁህ ነው።" ግንባሯ ላይ የአግድም መስመሮች ንግግሯን ተከትለው ብቅ አሉ።
" ታክሲ አገኘሁ ብለሀኝ? እሺ ፈጠን በል ---?"
ትውውቃቸው ገና የልጅ ዕድሜ ላይ ቢሆንም በተደጋጋሚ እሱን እሱን ማለቷ አልጣመውም ። እንድእህቱ ነው የሚያያት።
ፑል መጫወት አይችልም።ግን ሲጫወቱ ማየት በጣም ያስደስተዋል። ቀጠን ያለውን ቁመናው ግድግዳውን አስደግፎ አይኖቹ ከኳሶቹ ጋር ያንከራትታል ።
" ዳኛ ትሆናለህ? " ለስላሳ ድምፅ ---ከበጋ ሰማይ በላይ የጠራ ቅላፄ --- የትህትና ይሁን የሌላ ብቻ ደስ የሚል አቀራረብ።
" አይ እኔ መጫወት አልችልም። " ቃላቶቹ እንደ በቆሎ ፍሬ ተፈለፈሉ። ሳቅ አለች ። ተፍለቀለቀች ።
" መጫወት ሳይሆን ሲጫወቱ ማየት ያዝናናኛል ። " ደገመላት ።
"ተው ባክህ -----" ትስቃለች ። ቀይ በተቀለሙ ክብ እንጆሪ መሳይ ከንፈሮቿ መሃል ሐጫ የመሰሉ ጥርሶች የበለጠ አስዋቧት ።
" እዚህ ሰፈር ነህ ? " አጠር ያለች ---ቀይ ፊት ያላት ቆንጆ ነች።
" አይ---" ባጭሩ መለሰላት። አትኩሮ አያት---
" ሰላም እባላለሁ። " እጇን ስትዘረጋለት እንደ ቁልህ በተስተካከለ ፊቷ ላይ የብርሃን ፀዳል እየፈካ ታየው ---።
" እስክንድር " ተሰባስበው ፑል የሚጫወቱ ጎረምሶች መሃል ሆነው ወጋቸውን እየሰለቁ ቆዩ።ቤቱ የሙዚቃ ድምፅ ሞልቶታል።ሙዚቃውን ለመቀየር ተነስታ ሪሞቱን ጫን እያደረገች ትመርጥ ጀመር---- ድንገት ፈገግ አለች ። " ምነው ወደድከው? "
"አው ቴዎድሮስ ታደሰ ነፍሴ ነው። " ማስታወሻ ደብተር የያዘበት እጁ ከደረቱ እየለጠፈ። "ማየት ይፈቀዳል ? " አለችው ማስታወሻውን። በእምቢታ መለሰላት።
"ምን ያደርግልሃል ---? "
"ምንም ማስታወሻ ደብተር ነች ። " አላት። ገና ለገና ልቦናው ለ' ሰላም ' ያለውን ክፍት ቦታ ይሰጥ ዘንድ ይጠይቀዋል። ።አላቅማማም።
" እንዴት እስካሁን አላየሁሽም ። በተደጋጋሚ በዚህ እመላለሳለሁ። "
እኔ የሂርና ልጅ ነኝ። እዚህ ለስራ መጥቼ ነው። " ብላ ከመጨረሷ ስልኩ ጠራ ። ማንሳት አልፈለገም። " አንሳው እንጂ ? "
" አይ እንኪ የለም በይልኝ " ተርበተበተ። በግርምት ተቀበለችው።
"ሄ --ሄ --ሎ -"
" ማነሽ አንቺ ደግሞ --? "አስጠሊታ የማመናጨቅ ድምፅ ነበር።
" ይ--ቅርታ "
"የምን ይቅርታ ---እስክንድርስ --? ማነሽ--? " ጮሀች ።
" የለም ወጣ ብሏል። እኔ---" ተዘጋ ስልኩ። " ምንድነው እስክንድር ----"
"እሷ ተያትና ----ሂርና ነው ያልሽኝ--? " በደንብ ተግባቡ።
*** * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * *
የእስክንድር ሰፈር ሳብያን ቢሆንም በተደጋጋሚ 'ሠላም'ን ለማግኘት ወደ ለገሃሬ መሄዱን አልተወም።ሰላም ቀለል ያለች ልጅ ነች ።ቀን ከሷ ካሳለፈ ማታ ደግሞ ሲያነብና ሲፅፍ ያመሻል። ኪነ ጥበብ ይወዳል።በተለይ ግጥምና ሙዚቃ ያሰክሩታል።
" እኛ ሰዎች ቃላት ነን። ምድር ደግሞ ያልተፃፈበት ወረቀት ወይም ቃላቶች በትክክል ያልተሰደሩባት ንጣፍ ----ገጣምያን ደግሞ በዚህ ንጣፍ ላይ እንደ ዘበት የተዝረከረኩ የተፈጥሮ ስሜትን ፣ውበትን ና እይታዎችን እየከሸኑ የሚያስውቡ ስጋና አጥንት የለበሱ መላእክት ናቸው። " ይላል እስክንድር።
ጠዋት ጠባብ ክፍሉ ውስጥ እያነበበ ነበር።የጠዋት ፀሐይ በመስኮት ቀዳዳ አጮልቃ መፅሐፍ መደርደርያው ላይ አብርታለች። ስልኩ ጮሀች (እ ሪ ሪ ሪ ሪ አለች) ። በጣቱ ኮረኮማት። ሰላም ነበረች። አነሳው።
" ደህና ነኝ -ተጠፋፋን ? እሺ እመጣለሁ ---እሁድም ስለሆነ---እሺ-- እሺ-- ቻው። " ፊቱ ፈካ። ቀና ብሎ በጥቅስ ና በሚወዳቸው ጠቢባን ስዕል የተዋበውን የክፍሉ ግድግዳ ላይ አይኑን ጣለ።
"እውነት ረቂቁን ማግኘት ሳይሆን ተጨባጩን መኖር ነው። " የምትል ጎላ ያለች ጥቅስ ታየችው። ተነስቶ ቁርሱን በልቶ ትንሽ ካረፋፈደ በሁዋላ ወደ ሰላም ከነፈ።
* * *** * **************** *************** *******
ከታክሲ እንደወረደ ወደ ፑል ቤት ሲያመራ ከወትሮ በተለየ በረንዳው የጎረምሶች ዳና ሳይሆን አንዲት ቆንጆ ፀጉሯ ክምክም ጎፈሬ የሆነች ብፅእት-----ቁጭ ብላ ከፊት ለፊቷ ደግሞ የሲኒ መደርደርያ ከነጀበናው አስደማሚ ሕይወት ዘርተውበት ታየው። በፈገግታ ተቀበለችው። በጣም ደስ ብሎታል።
"ምነው እንቁጣጣሽ ነው እንዴ ? " እየሳቀ---በአይነ ቂጡ በፍቅር አይን እየገረመማት -----ከቆይታ በሁዋላ ደስ የሚል ጨዋታ እየተጫወቱ በመሃል-----
" ለቤተሰቦችሽ ስንተኛ ልጅ ነሽ? " ብሎ ጠየቃት። ነገረችው ። ቡናው ፈልቶ እየጠጡ ሳለ ጋብ ያለውን የጨዋታቸው ድባብ የናደ ጥያቄ ከወደ እስክንድር-----
" ምነው ትክዝ አልሽ----" ወድያው በምሽት ሰማይ ጎልተው የሚታዩ ከዋክብት የመሰሉ አይኖቿ የ እንባ ጠብታ አፍልቀው በብርቱካን መሳይ ጉንጭዋ አረጠቡት ። ደነገጠ ። ሊያረጋጋት ሞከረ። ቤተሰቧ ላይ የተፈጠረ አንዳች ረመጥ ሳያውቅ ነቅቶ እንደሆነ ጠረጠረ። እውነት ነው ።ቆይታ ሁሉንም አጫወተችው። እጅግ የሚያሳዝን የቤተሰቧ ታሪክ አሳልፋ በእምነት አወራችለት። ለቅሶዋ እንድታቆም ጠየቃት። በሁዋላ ላይ ወደ ቀድሞ ስሜቷ ብትመለስም---እስክንድር ግን በጣም ስሜቱ ተነክቶ ነበር።
ከተለያዩ በሁዋላ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ተገለባበጠ ። አሳዘነችው። ምሽቱ ገፍቶ 6 ሰዓት ሲሞላ የነገረችውን ሁሉ ለመፃፍ ተነሳ። አደረገውም ። ከ 3 ቀን በሁዋላ ደውላ ጠራችው። ሄደ።
" እዚህ አልቆይም---ቤተሰቦቼ ጋ ልሄድ ነው ። አንተን መተዋወቄ ደስ ብሎኛል። እንዳትረሳኝ ። ሰውነቱ ተዝለፈለፈ ። መቀበል አቃተው። ግና ግድ ነው። ከዝያ ቀን በሁዋላ ሠላምና እስክንድር በአካል ተለያዩ በመንፈስ ግን--------
ሰላም ማለት ለ እስክንድር በጠዋቱ ጊዜ እንደጤዛ አብራው የነበረች ግና የቀትር ፀሐይ መቋቋቋም ተስኗት ልቡ ውስጥ የቀረች ምልክት ናት።
ተፈፀመ በ ናሙስ ናኒ 14/05/2006